Ministry of Finance, Ethiopia

Ministry of Finance, Ethiopia

Government Administration

Addis Ababa, Arda Sub City Worda 6 25,001 followers

Welcome to the Official Linkedin Account of the Ministry of Finance #Ethiopia.

About us

Ministry of Finance is responsible for Public Finance Management, Macro Economy Policy Making, and Economic Cooperation.

Industry
Government Administration
Company size
1,001-5,000 employees
Headquarters
Addis Ababa, Arda Sub City Worda 6
Type
Government Agency
Founded
1908

Locations

  • Primary

    King George VI Street

    Arada Sub-City Woreda 06

    Addis Ababa, Arda Sub City Worda 6 1036, ET

    Get directions

Employees at Ministry of Finance, Ethiopia

Updates

  • በቻይና-አፍሪካ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች ላይ የሁለቱ ሀገራት ገንዘቦች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያስችል ስምምነት መደረሱን ገልፀዋል።

  • በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ስለሚከፈል የተጨማሪ እሴት ታክስ 1. የውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የኤሌክትሪክ እና የውሃ አቅርቦት ላለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ተደርጎ የነበረው አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን የወጪ ጫና ለማርገብና ለማቃለል ታስቦ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከአንድ ቤተሰብ ወርሃዊ አማካይ ፍጆታ በላይ ኤሌክትሪክ እና ውሃን በብዛት የሚጠቀመው የመክፈል አቅም ያለው የህብረተሰብ ክፍል በመሆኑ በተሰጠው መብት ይበልጥ ተጠቃሚ የሆነው ይህ የህብረተስብ ክፍል ነው፡፡ ይህ የህብረተሰብ ክፍል ታክሱ የሚያስከትልበት የወጪ ጫና ስለሌለ ድጋፉ ትርጉም አልነበረም፡፡ ድጋፉ ታሳቢ ያደረገውን የህብረተሰብ ክፍል ብቻ በሚጠቅም መልኩ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመሆኑ መብት ተፈጻሚ የሚሆነው የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሰረት የሚወሰን ከአንድ ቤተሰብ ወርሃዊ ፍጆታ ያልበለጠ የኤሌክትሪክ እና የውሃ ፍጆታ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህንን መጠን የሚወስን መመሪያ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወጥቶ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ስለዚህ መንግስት አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል በመኖሪያ ቤቱ የሚጠቀመውን አማካይ ወርሃዊ የውሃና ኤሌክትሪክ ፍጆታ ከታክሱ ነፃ የሚያደርግ ሲሆን ከታክሱ ነፃ ከተደረገው በላይ የውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ 2. የትራንስፖርት አገልግሎት በተመሳሳይ መልኩ እንደ ውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትራንስፖርት አገልግሎትም ላለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆን የተደረገው አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለትራንስፖርት የሚያወጣው ወጪ እንዳይንር እንዲሁም በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከፈለው ታክስ የዕቃዎችን ዋጋ መናር እንዳያስከትል በማሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ከህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ውጪ ለሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የዚህ አይነቱን ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ባለመሆኑ፣ መንግስት ማህበረሰቡ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትን እንዲጠቀም የተለያዩ ድጋፎችን በመስጠት እያበረታታና መሰረተ ልማቶችንም እየገነባ በመሆኑ ለትራንስፖርት አገልግሎት የተሰጠው ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመሆን መብት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር ከስምንት መቀመጫ በታች ያላቸውን ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንዳይመለከት ተደርጓል፡፡ ስለዚህ መንግስት አሁንም የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ያደረገ ሲሆን ባለሦስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር፣ አሽከርካሪውን ጨምሮ ከስምንት ሰው በታች የመጫን አቅም ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በመጠቀም የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፈልበት አድርጓል።

    • No alternative text description for this image
  • የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል መርሀ ግብር አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ፡፡ ነሐሴ 17 / 2016 ዓ.ም - የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሀ ግብር ላይ በመሳተፍ በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሜቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር አካባቢ አራንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ አረንጓዴ አሻራቸውን ካኖሩ በኋላ እንደገለጹት ላለፉት ተከታታይ አመታት በተካሄደው ሀገር አቀፍ አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀግብር የላቀ ሀገራዊ ንቅናቄና ህዝባዊ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ጠቁመው በዛሬው ዕለት በመላው ኢትዮጵያ በሚካሄደው በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል መርሀ ግብር ላይ የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ የማኖር አካል በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀ ግብር በሀገር ደረጃ ሁሉም ዜጎች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ መሆኑን ጠቅሰው ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋንን ማስፋት ምርትና ምረታማነትን በማሳደግ ለሀገር ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰውም በስፍራው ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

    • No alternative text description for this image
    • No alternative text description for this image
    • No alternative text description for this image
    • No alternative text description for this image
  • የተወሰኑ ሺህ የማይሞሉ ነጋዴዎችን ለመጠበቅ ስንል፤ በሀገር በቀል ነጋዴ ስም ሚሊዮኖችን የጎዳ የንግድ ሰርዓት ይዘን መቀጠል የለብንም፡፡ የንግድ ስርዓቱ ለውድድር ክፍት መሆን አለበት፡፡ ጎረቤት ሀገራት ያለ አንድ ዕቃ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ዕቃ ፤ የበለጠ የሚወደድበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ

    • No alternative text description for this image
  • በገንዘብ ሚኒስቴርና በተጠሪ ተቋማት የ2016 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም - በገንዘብ ሚኒስቴርና በተጠሪ ተቋማት የ2016 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ ላይ በሚኒስቴሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ የ2016 በጀት አመት አፈጻጸምና በ2017 በጀት ዓመት ተገባራዊ ለማድረግ የተያዘው የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ ዕቅድ ላይ በጉልህ ከተመላከቱት ዋናዋና ግቦች መካከል የዋጋ ንረትን ማረጋጋት፣ የመንግስት ገቢን ማሳደግ፣ የመንግስት የበጀት ጉድለት እና የእዳ ጫና እንዲቀንስ ማድረግ፣ ነቀፌታ የሌለበት የኦዲት ግኝት እንዲኖር መስራት፣ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን የበለጠ ማዘመን ፣ከልማት አጋሮች የውጭ ሀብት ግኝትና ፍሰትን ማሳደግ እንዲሁም በመንግስትና በግሉ አጋርነት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በተለየ ትኩረት እንዲፈጸሙ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል፡፡ የውይይት መድረኩን የመሩት የገንዘብ ሚነስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት በተጠናቀቀው የ2016 የበጀት ዓመት ከማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ጋር ተያይዞ በነበረው የዝግጅት ሂደት የገንዘብ ሚኒስቴር የማስተባበር ሚናውን በከፍተኛ ሃላፊነት እንደተወጣ አስታውሰው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ውጤታማ ለማድረግም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውና ሪፎርሙን ከማሳካት አኳያ የ2017 በጀት ዓመት እጅግ ወሳኝ ዓመት መሆኑን አሳስበዋል፡፡ ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘም በሁሉም ተቋማት የግልጽነትና ተጠያቂነት ስርዓትን በመዘርጋት መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ እንደሚገባ በመንግስት በተወሰነው መሰረት ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ ተገልጋዮችም ከበር ጥበቃ ጀምሮ ተገቢውን አክብሮት በመስጠት ያለምንም እንግልትና ውጣውረድ የሚፈልጉትን አገልግሎት አግኝተው የሚስተናገዱበት ስርዓት እንደሚረጋገጥም ክቡር ሚነስትሩ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው እንደገለጹት ወቅቱ  ወደ ተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የገባንበት በመሆኑ የ2017 የበጀት ዓመት የኢትዮጵያን ቀጣይ የዕድገት ጎዳናና ሽግግር የሚወስን የተለየ አመት ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም የተጀመረው ሪፎርም በሃምሳ አመት አንዴ የተከሰት መጠነ ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም መሆኑን በመገንዘብ በበጀት አመቱ ከሚኒስቴሩና ከተጠሪ ተቋማት የላቀ አፈጻጸም እንደሚጠበቅ ዶ/ር ኢዮብ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በአዲሱን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም መሰረት በቀጣይ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ የሚታወጀውን ተጨማሪ በጀት ተክትሎ  የመንግስት የገቢና ወጭ ዕቅድ ሲከለስና በዛሬው ዕለት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት የሚኒስቴሩ ዕቅድ ላይም ክለሳ እንደሚደረግበትም ተብራርቷል፡፡

    • No alternative text description for this image
    • No alternative text description for this image
    • No alternative text description for this image
    • No alternative text description for this image
    • No alternative text description for this image

Similar pages