Ethiopian Medical Association’s Post

የኢትዮጵያ የቆዳና አባላዘር ህክምና ማህበር አመታዊ ጉባኤ "ለውበት መጠበቂያ ሲባል የሚሰጠው የቆዳ ህክምና እና ተግዳሮቶቹ" በሚል ተካሂዷል። በጉባኤውም በዘርፉ የተስተዋሉ ውጤቶችና ተግዳሮቶች ተዳሰዋል። በጤና ሚኒስቴር ጤናና ጤና ነክ ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል በጉባኤው ላይ በመገኘት የቆዳና አባላዘር ህክምና መተዳደሪያ አዋጅ፤ ደንብና ስታንዳርድ ያላቸው ቢሆንም ለአገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ በስታንዳርዱ መሰረት ደህንነቱና ጥራቱ የተረጋገጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የተጠናከረ ስራ መሰራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ የቆዳና ሌሎች የአባላዘር ህክምና በሽታዎች ህክምና እንደሃገር ፍላጎት ያለበት የህክምና ዘርፍ በመሆናቸው ማህበረሰቡን ባማከለ መልኩ ተደራሽነትን ማስፋት እንደሚያስፈልግ አቶ እንዳልካቸው ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የደረጃ ዝግጅት መሪ ስራ ስፈፃሚ የሆኑት አቶ ይልማ ንጉሴ በአመታዊ ጉባኤ ላይ በመገኘት የጤናው ሴክተር በዓለማችን በተለየ መልኩ ቁጥጥር የሚደረግበት ዘርፍ ነው፡፡ ሃገራችንም ከውበት ሳሎኖች፤ ከኮስሞቲክስ ግብዓቶች፤ ከተለያዩ መቀመሚያ ኬሚካሎች፤ አገልግሎቱን ከሚሰጡ ባለሙያዎች እና የመሳሰሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች አስቻይ የሆነ የቁጥጥር ማዓቀፍ ቢኖርም ጤና ሚኒስቴር፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ማህበር እና ከዘርፉ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸው ባለድርሻ አካላት ክፍተት በሚታይባቸው ጉዳዮች ላይ በመምከር ዘርፉን ማጠናከር እንደሚስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የቆዳና አባላዘር ህክምና ማህበር ሊቀ-መንበር ዶ/ር ሽመልስ ንጉሴ ለውበት መጠበቂያ ሲባል የሚሰጠው የቆዳ ህክምና እና ተግዳሮቶቹ በሚል የተዘጋጀው የ11ኛ ዓመት ጉባኤ የተለያዩ ሃገራትን ልምድ የቀሰምንበትና ከሚመላከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የመከርንበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለማህበረሰባችን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በትክክለኛው ባለሙያ መሰጠት የሚያስችል አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚችል ተስፋቸውን መግለጻቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

  • No alternative text description for this image
  • No alternative text description for this image
  • No alternative text description for this image
  • No alternative text description for this image

To view or add a comment, sign in

Explore topics